Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በግብዓት እጥረት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የተሽከርካሪ ሰሌዳ ከነገ ጀምሮ ይሰጣል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ በግብዓት እጥረት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የኮድ- 2 ተሽከርካሪዎች ሰሌዳ አገልግሎት ከነገ ጀምሮ እንደሚሰጥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣኑ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የኮድ -2 አ.አ ሰሌዳ በግብዓት እጥረት ምክንያት አትሞ እያስረከበ ስላልሆነ የሰሌዳ እጥረት ያጋጠመ መሆኑን ግንቦት 6 ቀን 2014 ዓ.ም ማሳወቁ ይታወሳል፡፡
ስለሆነም የነበረው የሰሌዳ ምርት እጥረት በመፈታቱ የኮድ -2 አ.አ ሰሌዳ ፈላጊዎች ከነገ ጀምሮ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
በዚህም ተገልጋዮች ወይም የኮድ 2 ሰሌዳ ፈላጊዎች በሙሉ መሟላት ያለባቸውን መረጃዎች በማሟላት በ11ዱም ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች በመኖሪያ አድራሻቸው ብቻ መስተናገድ እንደሚችሉ የባለስልጣኑ መረጃ አመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version