አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጋላፊ እስከ ሰርዶ በየመንገዱ ዳር ተደብቆ የቆዩት 15 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በተጨማሪም አንድ ቦቴ ጫካ ውስጥ ነዳጅ ሲቀዳ እጅ ከፍንጅ ተይዟል፡፡
ዘመቻ ከተጀመረ ጌዜ ጀምሮ በየቦታው ተደብቀው የቆዩ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች መንቀሳቀስ መጀመራቸው ተመላክቷል፡፡
በዚህም ባለፉት ሦስት ቀናት በነዳጅ እጥረት ምክንያት ተዘግቶ የነበሩ የሰመራ ነዳጅ ማደያዎች ሥራ ጀምረዋል ሲል የአፋር መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!