አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራዎችን ለማስቀጠል በቅንጅት መስራት ይገባል ሲሉ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ጀነራል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ፡፡
ዳይሬክተር ጀነራሉ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የህልውና ጉዳይ መሆኑን ለተቀረው ዓለም ለማስረዳት የተደረጉ ጥረቶች አበረታች እንደነበሩ አብራርተዋል ፡፡
ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራዎችን እውን ለማድረግ ክፍተቶችን ማረቅ አለብን ያሉት አምባሳደሩ÷በተለይም መረጃን ለሚፈልጉ አካላት በወቅቱ ማድረስ ይገባል ነው ያሉት፡፡
በአባይ ጉዳይ ላይ በግላቸው አገራቸውን ወክለው የሚሟገቱት ጀማል በሽር እና የዓረቢ ሚዲያ የኢትዮጵያ ወኪል ጋዜጠኛ ሰኢድ ሙዘይን በበኩላቸው÷የኢትዮጵያን እውነታ ለማስረዳት የተከናወኑ ስራዎች አበረታች ውጤት እንደታየባቸው ተናግረዋል፡፡
አሁን የህዳሴው ግድብ ሶስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት የሚከናወንበት ዋዜማ በመሆኑ የግብጽ የተለመደ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ መቀጠሉንም ገልጸዋል፡፡
ይህን የሚመጥን እና የኢትዮጵያን እውነታ ለተቀረው ዓለም የማስረዳቱ ጠንካራ ስራ በቀጣይ እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል፡፡
በተለይም የግብጽን ተቀያያሪ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ መመከት ይቻል ዘንድ የተቀናጀ አሰራሮችን መተግበር እንደሚገባ መቀመጫውን ለንደን ያደረገው አል ዓረቢ ሚዲያ የኢትዮጵያ ወኪል ጋዜጠኛ ዛይድ ዘይዳን ተናግሯል፡፡
ተቀራርቦ በቅንጅት በመስራት ዘላቂ የዲፕሎማሲ ስራዎች ላይ ማተኮር እንደሚገባም ጋዜጠኞቹና የአባይ ውሃ ጉዳይ ተሟጋቾቹ አስገንዝበዋል፡፡
በአወል አበራ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

