አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2012 ፣ (ኤፍ ቢ ሲ) በቡርኪና ፋሶ በአንድ መንደር ላይ ተፈፀመ ጥቃት 43 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ፡፡
ታጣቂዎች ቡርኪና ፋሶ ከማሊ ጋር በምትዋሰንበት ሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል በርካቶችን ሲገድሉ ስድስት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን መንግስት ገልጿል፡፡
ማንነታቸው ያልታወቁት ታጣቂዎቹ ዲንጉይላ እና ባርጋ በተባሉ ሁለት የየታንጋ ግዛት መንደሮች ጥቃቱን መፈፀማቸው ነው የተነገረው።
ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር በተለያዩ ሀገሪቱ ክፍሎች በታጣቂዎች በሚፈፀሙ ጥቃቶች የበርካታ ዜጎቿ ህይወት እያለፈ ይገኛል።
በፈረንጆቹ 2019 ቡርኪና ፋሶ፣ ማሊና ኒጀር በተፈፀሙ ጥቃቶች ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ ያመለክታል፡፡
ምንጭ÷አልጀዚራ

