Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፋኦ የበረሃ አንበጣን ለመከላከል ለኢትዮጵያ የአውሮፕላን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 1፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአለም የምግብና እርሻ ድርጀት( ፋኦ) በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ ለመከላከል የአውሮፕላን ድጋፍ አደረገ፡፡

የአውሮፕላን ድጋፉ ርክክቡ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ካባ ኡርጌሳ በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

በዚህ ወቅት ሚኒስትር ዴኤታው÷ መነሻውን ከየመንና ሱማልያ ሀገራት አድርጎ ወደ ሀገሪቱ የገባው የበረሃ አንበጣ የመከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአለም የምግብና እርሻ ድርጀት ይህንን ስራ ለማገዝ ተጨማሪ የአውሮፕላን ድጋፍ ማድረጉ የመከላከል ስራውን ይበልጥ ውጤታማ ያደርገዋል ብለዋል።

በቀጣይም ተጨማሪ አውሮፕላኖች ወደ ስራ በማስገባት ሰፊ የመከላከል ስራ ለመስራት እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን መጠቆማቸውን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Exit mobile version