Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራቱ ህንጻዎችን ለማሞቅ እና ለማቀዝቀዝ የሚጠቀሙትን ጋዝ እንዲቀንሱ ሊጠይቅ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን በቀጣይ ሣምንት ሀገራቱ ለቁጠባ ሲባል ህንጻዎችንም ሆነ ቢሮዎቻቸውን ለማሞቅ እና ለማቀዝቀዝ የሚጠቀሙትን ጋዝ መጠን እንዲቀንሱ ሊጠይቅ መሆኑን ኤ ኤፍ ፒ ተመለከትኩት ያለውን ሠነድ ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

ኮሚሽኑ የሩሲያ የጋዝ አቅርቦት አስተማማኝ ስላልሆነና በማንኛውም ጊዜ ሙሉ በሙሉ ሊቋረጥ ስለሚችል ሁኔታዎችን በተሻለ መልኩ ለመቋቋም ሀገራቱ የኃይል መጠን ፍላጎታቸውን እንዲገድቡ በቀጣዩ ሳምንት ሊጠይቅ መሆኑን ዘገባው አመላክቷል።

ሠነዱ የህዝብ መገልገያ ሕንፃዎች ከ19 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በማይበልጥ የሙቀት መጠን እንዲሞቁ እና ከ25 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በማያንስ እንዲቀዘቅዙ ምክረ ሃሳብ አስቀምጧል፡፡

የሕንጻዎችን የሙቀት መቆጣጠሪያ በአንድ ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ዝቅ በማድረግ ለጋዝ የሚወጣውን ክፍያ በ10 በመቶ መቀነስ እንደሚቻል ሲ ጂ ቲ ኤን የኃይል ባለሙያዎችን አስተያየት ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version