Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በአሸባሪው ህወሓት የወደሙ የትምህርት ተቋማት ግንባታን ለማስጀመር ኮምቦልቻ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለና የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ ሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በአሸባሪው ህወሓት ወረራ የወደሙ የትምህርት ተቋማት ግንባታን ለማስጀመር ኮምቦልቻ ከተማ ገብተዋል።
የሥራ ኃላፊዎቹ ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አብዱ ሁሴን፣ የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ፣ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መሐመድ አሚን የሱፍን ጨምሮ ሌሎች የዞንና ከተማ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ዶክተር ይልቃል እና ፕሮፌሰር ብርሃኑ በአካባቢው በሚኖራቸው ቆይታ÷በደቡብ ወሎ ዞንና በደሴ ከተማ በአሸባሪው ህወሓት ወረራ የወደሙ የትምህርት ተቋማትን የመልሶ ግንባታ መርሐ ግብር በይፋ ያስጀምራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከደቡብ ወሎ ዞን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version