Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከመተማ -ገላባት ያለው የኢትዮ-ሱዳን ደረቅ ወደብ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመተማ -ገላባት ያለው የኢትዮ-ሱዳን ደረቅ ወደብ በዛሬው ዕለት ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቢክስ ወርቄ የደረቅ ወደቡ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን በተመለከተ ባደረጉት ንግግር÷ በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ዘመናትን ያስቆጠረው ወንድማማችነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም ኢትዮጵያዊና የአካባቢው ማህበረሰብ የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።
ከድንበር መዘጋት ጋር ተያይዞ የነበረው ችግር የኢትዮጵያ መንግሥት ባስቀመጠው በሰላማዊ አማራጭ በውይይት የመፍታት አካሄድን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
የውስጥ ችግራችንን በማጤን ሰላማችንን በማደፍረስ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማበላሸት ለሚሠሩ ኃይሎች መጠቀሚያ ከመሆን መቆጠብ ይገባል ማለታቸውንም አሚኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version