Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ ህገ ወጥ ሽጉጥ እና ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረጉት ክትትል ህገ ወጥ ሽጉጥና ጥይት መያዛቸውን አስታወቁ ፡፡

በቅንጅት በተደረገው ክትትል ሊፋን 620 በሆነ የቤት መኪና ውስጥ 31 ሪታይ ፋልኦን ሽጉጥ፣ 490 የኢኮልፒ እና 94 የስታር ጥይት ከአምስት የሽጉጥ ካርታ ጋር ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በቀጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል፡፡

በተሽከርካሪው አካል ላይ መሸሸጊያ በማዘጋጀት ከሌሎች እቃዎች አመሳስሎ በመጫን የጦር መሳሪያዎቹን ወደ አዲስ አበባ ለማስገባት የሞከሩ ግለሰቦች በክትትል እየተያዙ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ከተለያዩ አቅጣጫዎች ድንበር አቋርጠው ወደ ከተማዋ የሚገቡ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች ላይ የሚደረገው ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ፖሊስ ገልጿል፡፡

ህብረተሰቡም ጥቆማ መስጠቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ መልዕክት ማስተላለፉን ከከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ፅህፈት ቤት ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት ጋር በመተባበር ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ህገወጥ የጦር መሳሪያና ተተኳሽ ጥይት በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተገልጿል።

በዚህም 4 ሺህ 100 ተኳሽ የክላሽ ጥይት ፣ 4 ኮፋ ፣ 14 የክላሽ ካዝና ፣ አምስት የተለያየ የባንክ ደብተር ፣ 28 ሺህ ጥሬ ገንዘብ እንዲሁም የተለያዩ ስልኮች መያዛቸውን ከከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version