አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ያሰለጠናቸውን 104 ከፍተኛና መካከለኛ መኮንኖች አስመርቋል።
የምረቃ ስነስርዓት ላይ ተገኝተው ማዕረግ ያለበሱትና የስራ መመሪያ የሰጡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ናቸው።
በተጨማሪም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፈቲያ አደን ጨምሮ ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ ወርሰሜ እና የካቢኔ አባላት በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላመጡት መኮንኖች ሽልማቶችን አበርክተዋል።
በስነ ስርዓቱ ላይ የአገር ሽማግሌዎች፣ ዑጋዞች፣ አባገዳዎች፣ ነዋሪዎች እና የተመራቂ ቤተሰቦች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛና መካከለኛ የፖሊስ መኮንኖችን በራሱ አቅም አስተምሮ ሲያስመርቅ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!