አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን በተገኙበት የ2014 ዓ.ም የፖለቲካና የውስጠ ድርጅት ስራ አፈጻም ሪፖርትን እየገመገመ ነው፡፡
አቶ አሻድሊ በ2014 በጀት ዓመት የታዩ ክፍተቶች በ2015 ዓ.ም እንዳይደገሙ ለማስቻል ስራ አፈጻጸሙ በአስተባባሪ ኮሚቴና በስራ አመራር ኮሚቴ ደረጃ በጋራ ዳግም እንዲገመገም መደረጉን አንስተዋል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር በበኩላቸው÷በአፈጻጸም ሂደት ጥንካሬው እንደተጠበቀ ሆኖ በአመራር ደረጃ የሚታዩ ክፍተቶች በቶሎ መታረም እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
በመድረኩ በፖለቲካ፣ በአደረጃጀት፣ በህዝብ ግንኙነት፣ በገቢና ፋይናንስ፣ በትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የተሰሩ ስራዎችን በጥንካሬና በድክመት በመለየት በቀጣይ ድክመቶች የሚታረሙበት አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!