አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በዩክሬን ኦዴሳ ወደብ በሚገኝ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ማዕከል ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል፡፡
በክሩዝ ሚሳኤል በተፈጸመው ጥቃትም÷ ከምዕራባውያን ለዩክሬን በስጦታ የተበረከቱ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ማውደም መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡
ከአሜሪካ ለዩክሬን የተሰጠ “ሃርፖን” የተሰኘ ጸረ ሚሳኤል እና የዩክሬን ጦር መርከብ በጥቃቱ ከወደሙት የጦር መሳሪያዎች መካከል መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
ሚኒስቴሩ ትናንት በኦዴሳ ወደብ ላይ የተፈጸመው ጥቃት “ንጹሃን ዜጎችን ኢላማ ያደረገ ነው” በሚል ከዩክሬን እና አጋሮቿ የቀረበውን ክስ መሰረተ ቢስ ውንጀላ ሲል አጣጥሎታል፡፡
በኦዴሳ ወደብ የተፈጸመው የሚሳኤል ጥቃት ዩክሬን የእህል ምርቷን በጥቁር ባህር በኩል ለውጭ ገበያ እንድታቀርብ የሚያስችል ስምምነት ከሩሲያ ጋር ከተፈራረመች ከአንድ ቀን በኋላ ነው፡፡
ይህ ሁኔታም ዩክሬን የእህል ምርቷን በጥቁር ባህር በኩል ለውጭ ገበያ እንድታቀርብ የተያዘውን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ አስቸጋሪ ሊያደርገው ይችላል የሚል ስጋት መፍጠሩን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!