Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኢራቅ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ላይ በተፈጸመ ጥቃት የአሜሪካ እና እንግሊዝ ወታደሮች ተገደሉ 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢራቅ በሚገኝ የብሪታንያ እና አሜሪካ ወታደራዊ ካምፕ ላይ በተፈጸመ የሮኬት ጥቃት ሁለት ወታደርና አንድ ተቋራጭ ተገደሉ።

በጥቃቱ ለህልፈት የተዳረጉት አንድ የአሜሪካ ወታደርና ተቋራጭ እንዲሁም አንድ የእንግሊዝ ወታደር መሆናቸው ተገልጿል።

በተፈጸመው ጥቃት ህይወታቸው ካለፈው በተጨማሪ 12 ሰዎች መቁሰላቸውም ነው የተገለጸው።

በኢራቅ እና ሶሪያ በአሜሪካ የሚመራው ጥምር ጦር ወታደራዊ ካምፑ ላይ 18 የሮኬት ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።

እስካሁን ድረስ ለጥቃቱ  ሃላፊነት የወሰደ አካል አለመኖሩም ነው የተነገረው።

አሜሪካ በበኩሏ ከዚህ ቀደም በኢራቅ ለተፈጸሙ ጥቃቶች በኢራን የሚደገፉ ታጣቂዎችን ስትኮንን ቆይታለች።

አሜሪካ የኢራኑን ከፍተኛ የጦር አዛዥ ቃሲም ሱሌይማኒን ከገደለች ወዲህ በሁለቱ ሀገራት መካከል ውጥረቱ ነግሷል።

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Exit mobile version