አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ በተከሰተው ከፍተኛ የአየር ሙቀት ምክንያት የሰደድ እሳት በፍጥነት እየተስፋፋ መምጣቱና በጤናም ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ መሆኑ ተነገረ፤
በአሜሪካ በካሊፎርኒያ ዮሴሚት ብሔራዊ ፓርክ አቅራቢያ ከፍተኛ የሆነ የሰደድ እሳት በፍጥነት መስፋፋቱን ተከትሎ በአካባቢው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል።
ክስተቱ ለአካባቢው ነዋሪዎች የጤና ስጋት ማስከተሉም ተገልጿል፡፡
በሺዎች በሚቆጠር ሄክታር መሬት ላይ እየተስፋፋ የሚገኘው የሰደድ እሳት ከ6 ሺህ በላይ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ማስገደዱ ተነግሯል።
የካሊፎርኒያ በሰደድ እሳት መንደድ አብዛኛው የአገሪቱ ክፍል በሙቀት ማዕበል እንዲናወጥ አድርጎታልም ተብሏል፡፡
ችግሩን ተከትሎ በተቀሩት የሀገሪቱ ግዛቶች የማስጠንቀቂያ መልዕክቶች በስፋት እየተላለፉ እንደሆነም የሲጂቲኤን ዘገባ አመላክቷል፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!