Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ሙስጠፌ በፌርፌር ወረዳ አሸባሪውን አልሸባብ እየተፋለሙ የሚገኙ የልዩ ሃይል አባላትን አበረታቱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ በሶማሊያ ድንበር ፌርፌር ወረዳ አሸባሪውን አልሸባብ እየተፋለሙ የሚገኙ የክልሉ ልዩ ሃይል አባላትን ጎብኝተዋል፡፡
አቶ ሙስጠፌ በትናንትናው ዕለት ከፌርፌር ወረዳ 15 ኪሎ ሜትር በስተ ሰሜን በኩል ለመግባት የሞከረው አሸባሪውን የአልሸባብ ቡድን የደመሰሰውን የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ምስጋና በማቅረብ አበረታተዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ከወረዳው የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ነው የተገለጸው፡፡
በጉብኝት መርሐ ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች መሳተፋቸውን ከሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version