አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት በዛሬው እለት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ የተለያ ሹመቶችን አጽድቋል።
የክልሉ ምክር ቤት የ5ኛ ዓመት 5ኛ የሥራ ዘመን 5ኛ አስቸኳይ ጉባዔውን በዛሬው እለት ማካሄዱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመለክታል።
በአስቸኳይ ጉባዔውም በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የቀረቡለትን ጨምሮ የተለያዩ ሹመቶችን መርምሮ አጽድቋል።
በዚህ መሰረት፥
1. አቶ ታደለ ተረፈ – የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ
2. አቶ ጌታሁን አብዲሳ – የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር
3. አቶ ነጂመዲን አልሃዲ – የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት
4. አቶ ሉቅማን አብዱልቃድር – የክልሉ ምክር ቤት የከተማ ልማት፣ ንግድ፣ ኢንዱስትሪ፣ ትራንስፖርት እና የበጀት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው ተሾመዋል።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው የተሾሙት አቶ ጌታሁን አብዲሳ በክልሉ በተለያዩ ተቋማት በኃላፊነት ያገለገሉ ሲሆን፣ ወደዚህ ኃላፊነት እስከመጡበት ጊዜ ድረስም በኢፌዴሪ ሠራተኛ እና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው አገልግለዋል።

