አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በኮሎምቢያ ካሊ በሚደረገው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፉ አትሌቶች ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡
የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድኑ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ላይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማሪፊያ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተወካዮች በተገኙበት ሽኝት ተደርጎለታል፡፡
በኮሎምቢያ ካሊ የሚደረገው ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ከነሃሴ 1 እስከ 6 ባሉት ጊዜያት የሚደረግ መሆኑን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡