አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር የ2014 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት እያቀረቡ ነው፡፡
የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ፈቲያ አደም እንደተናገሩት፥ ጉባኤው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ቻርተርን በሚመለከት ውይይት ያካሂዳል።
በተጨማሪም የድሬዳዋ አስተዳደር መገናኛ ብዙሃን ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2014 የስራ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2015 ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ከተካሄደበት በኋላ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል፡፡
ምክር ቤት ለሁለት ቀናት በሚኖረው በጉባዔ÷ የሚቀርቡለትን የተለያዩ አዋጆች፣ የአስተዳደሩ የ2015 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት እንዲሁም የተለያዩ ሹመቶችን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡
በተሾመ ኃይሉ
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!