Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በየቤተ-ዕምነቱ የምሥጋና መርሐ -ግብር መዘጋጀቱን አስታወቀ

አዲ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የምሥጋና ጥሪ ተከትሎ በየቤተ-ዕምነቱ የምሥጋና መርሐ -ግብር መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡

የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ዋና ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ኢትዮጵያ ታመሥግን” የሚል ጥሪ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ መርሁ ከጉባዔው መርህና ተልዕኮ ጋር የሚዛመድ በመሆኑ ቅቡልነት እንዳለው ገልጸዋል።

በዚህም የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔው በየቤተ ዕምነቱ የምሥጋና መርሐ-ግብር መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

በዚህም የፊታችን ዓርብ በመላው ኢትዮጵያ በእስልምና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ የጁምዓ ሶላት ላይ ሁሉም 3 ደቂቃ ለምሥጋና እንዲሰጥና የሃይማኖት አባቶችም ይህን እንዲያስፈጽሙ ጉባዔው ጥሪ አቅርቧል።

ቅዳሜ ሐምሌ 23 የኢትዮጵያ አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን አማኞችም በአምልኮ መርሐ ግብራቸው ሰዓት ለ3 ደቂቃ ፈጣሪያቸውን እንዲያመሠግኑ እንዲሁም ዕሁድ ሐምሌ 24 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች ኅብረት፣ የኢትዮጵያ መካነ-ኢየሱስ እና የኢትዮጵያ ቃለ-ሕይወት ቤተክርስቲያን በአምልኮ መርሐ-ግብራቸው በተመሳሳይ ለ 3 ደቂቃ የምሥጋና መርሐ-ግብር መዘጋጀቱን ቀሲስ ታጋይ በመግለጫቸው ጠቁመዋል።

በሃይማኖት ኢያሱ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version