አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን በ3ኛ መደበኛ ጉባዔው ልዩ ልዩ አዋጆችን ተወያይቶ አጽድቋል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አብዬ ካሳሁን የተሻሻሉ አዋጆች እንዲጸድቁ ለምክርቤቱ አቅርበዋል።
ለምክር ቤቱ የቀረቡ አዋጆችም “የተሻሻለው የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ” እና “የተሻሻለው የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ማቋቋሚያ አዋጅ” ናቸው።
ምክር ቤቱም ሁለቱንም ረቂቅ አዋጆች የተሰጡ ማስተካከያዎችን ጨምሮ በአብላጫ ድምጽ ማፅደቁን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!