አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሚያደርገውን የኤርባስ A350-1000 ትዕዛዝ ከኤርባስ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ ጋር ተፈራርሟል።
አየር መንገዱ ከዚህ በፊት 22 ኤርባስ A350-900 አውሮፕላን በማዘዝ 16ቱን ተረክቦ ስራ ላይ ማዋሉን አስታውቋል፡፡
ከተቀሩት የኤርባስ A350-900 አውሮፕላን ትዕዛዞች አራቱ ወደ ኤርባስ A350-1000 እንዲቀየሩ ከኤርባስ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ ጋር ስምምነት መደረጉን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህ ስምምነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ A350-1000ን አገልግሎት ላይ ያዋለ የመጀመሪያው የአፍሪካ አየር መንገድ እንደሚያደርገው ተጠቁሟል፡፡

