Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከጋራ ገቢዎች ከ34 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ለክልሎች መተላለፉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራልና የክልል መንግሥታት የጋራ ገቢዎች ተብለው ከተወሰኑት የታክስ አይነቶች ከ34 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ለክልሎች መተላለፉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በ2014 በጀት ዓመት በተቀመጠው የገቢ ማከፋፈያ ቀመር መሠረት 34 ቢሊየን 692 ሚሊየን 318 ሺህ 500 ብር ለክልሎች እንዲተላለፍ መደረጉን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ገልጸዋል፡፡

የሚተላለፈው የብር መጠን ከጊዜ ወደጊዜ ከፍተኛ እድገት እያሳየ መምጣቱን የጠቆሙት ሚኒስትሩ ÷ የማከፋፈያ ቀመር ከመሻሻሉ በፊት በ2012 በጀት ዓመት ከ4 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ቀመሩ ከተሻሻለ በኋላ ባሉ ተከታታይ ዓመታት ደግሞ በ2013 ዓ.ም ከ22 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ እና በዘንድሮው በጀት ዓመት ከ34 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ እንዲተላለፍ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

የማከፋፈያ ቀመሩ መሻሻል የገቢ አሰባሰቡን አቅም መጨመሩ እና ክፍፍሉ በተቀመጠው ቀመር መሠረት መሠራቱ ለሚተላለፈው ገቢ ዕድገት ዋነኛ ምክንያቶች እንደሆኑ መገለጹን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version