Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አምባሳደር ስለሺ በቀለ ከተለያዩ የአሜሪካ ህግ አውጪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2014 (ኤፍ ቤ ሲ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከተለያዩ የአሜሪካ ሴናተሮችና ህግ አውጪዎች ጋር ተወያይተዋል።
አምባሳደር ስለሺ ከሴናተር ቴድ ክሩዝ፣ ከኮንግረስ አባሎቹ ቻክ ፍሌይሽማን፣ ጁሊያ ሌትሎው፣ ዳሬል ኢሳ፣ ክሪስ ስሚዝ እና ስቲቭ ዎማክ ጋር ነው በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የመከሩት፡፡
በውይይታቸውም አምባሳደር ስለሺ÷የኢትዮጵያ መንግስት በግጭት እና ድርቅ ሳቢያ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች እያደረገ ስላለው ሰብዓዊ ድጋፍ እና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ስለሚከናወኑ ተግባራት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በተጨማሪም በኢትዮጵያ እየተከናወኑ በሚገኙ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ልማቶች እንዲሁም አሸባሪው አልሸባብ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ላይ ስለጸመው ትንኮሳና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የአሜሪካ ህግ አውጪዎች በበኩላቸው÷ኢትዮጵያ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታን ለማዳረስ እያደረገችው ላለው ጥረት እውቅና መስጠታቸውን በአሜሪካ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከዚህ ባለፈም የፌዴራል መንግስት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት በሰላም ውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እያሳየ ያለውን ቁርጠኝነት ማድነቃቸው ተጠቁሟል፡፡

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version