Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሚዛን አማን ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን አማን ከተማ በደረሠ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
 
የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ መረጃና ስታቲስቲክስ ማስተባበሪያ ክፍል ሀላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ይመኙሻል ክፍሌ እንደገለጹት÷ አደጋው የደረሰው በሚዛን አማን ከተማ ሸኮ በር አካባቢ ከሚዛን ወደ አማን በመጓዝ ላይ የነበረ የጭነት አይሱዙ መኪና ለጥገና ጋራጅ ከቆመ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ጋር በተፈጠረ ግጭት ነው፡፡
 
በተፈጠረው አደጋም ለጥገና በቆመው መኪና አጠገብ የነበሩ ሁለት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ÷ በአንድ ሰው ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ኢንስፔክተሯ ገልጸዋል።
 
የአደጋው መንስኤ ገና እየተጣራ ነው ያሉት ኢንስፔክተሯ÷ መሰል አሳዛኝ አደጋዎችን ለመከላከል ህብረተሠቡም ሆነ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰባቸውን ደሬቴድ ዘግቧል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
Exit mobile version