አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በንግድ ማጭበርበርና በኮንትሮባንድ መንግስት ሊያጣው የነበረን ከ50 ቢሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች የተቋሙን የ2014 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ገምግመዋል፡፡
በዚህም የጉምሩክ ኮሚሽን በ2014 በጀት ዓመት በንግድ ማጭበርበርና በኮንትሮባንድ መከላከል በሰራው ጠንካራ የቁጥጥር ስራ መንግስት ሊያጣው የነበረን 50 ቢሊየን 46 ሚሊየን 954 ሺህ 335 ብር ከ57 ሳንቲም ማዳን ተችሏል ተብሏል፡፡