Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ በ4ኛው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስካሁን 9 ነጥብ 8 ሚሊየን ችግኝ ተተክሏል – አቶ ጥራቱ በየነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ በአራተኛው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስካሁን 9 ነጥብ 8 ሚሊየን ችግኝ መትከል መቻሉን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ገለጹ፡፡
 
አቶ ጥራቱ ዛሬ የዘንድሮውን የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አፈፃፀምን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጽህፈት ቤታቸው ገምግመዋል፡፡
 
በግምገማ መድረኩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ4ኛው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስካሁን 9 ነጥብ 8 ሚሊየን ችግኝ መትከል መቻሉ ተመላክቷል፡፡
 
በዚህም የእቅዱን 76 በመቶ ማሳካት መቻሉን ጠቁመው÷ ለአራተኛው ዙር የችግኝ ተከላ ስኬት ነዋሪው በጋራ በመረባረብ ታሪካዊ ለትውልድ የሚተላለፍ አሻራ የማኖር ሃላፊነቱን እንዲወጣም ነው ጥሪ ያቀረቡት።
 
በከተማዋ በቅርቡ በአንድ ጀምበር 4 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ለተያዘው እቅድ ስኬት ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ዝግጅት በአፋጣኝ ሊያጠናቅቁ እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን ከጽህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።
 
በከተማዋ የሃይማኖት ተቋማት፣ የፀጥታ አካላት፣ ወጣቶችና ሴቶች ፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ፣ በጎ ፈቃደኞች፣ የሲቪክ ማህበራት ባለሃብቶችና ሁሉም ዜጎች የአረንጓዴ አሻራቸውን ከባለፉት ጊዜያት በተሻለ በማኖር የለመለመች ኢትዮጵያን ለትውልድ የማስረከብ ሃላፊነት እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version