አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2014 በጀት ዓመት የሴክተር የጋራ ጉባዔ “በፈተናዎቻችን ሳንበገር ስኬቶቻችንን እያሰፋን ለላቀ ውጤት እንተጋለን” በሚል መሪ ቃል በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በውይይቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬን ጨምሮ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና ማህበራዊ ልማት ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የተቋሙ አመራሮች፣ የክልል ቢሮ ሃላፊዎች፣ የሲቪክ ማህበራት አመራሮች እንዲሁም የተለያዩ የፌዴራል ተቋማት ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በጉባዔው የ2014 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2015 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት በማካሄድ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

