Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአፋር ክልል የክረምት በጎ ፈቃድ መርሐ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ200 ሺህ በላይ ወጣቶች ተሳትፎ ያደርጉበታል የተባለው የአፋር ክልል የክረምት በጎ ፈቃድ መርሐግብር ዛሬ ተጀምሯል፡፡

በመርሐ ግብሩ መክፈቻ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አስያ ከማል፣ የክልሉ አመራሮች እና የምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።

ለሁለት ወራት በሚቆየው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ200 ሺህ በላይ ወጣቶች እንደሚሳተፉ የአፋር ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

ወጣቶቹ በአረንጓዴ ልማትና ክብካቤ፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የአካባቢ ጽዳት፣ ደም ልገሳና ተያያዥ የሕብረተሰቡን ችግር የሚፈቱ ስራዎችን እንደሚያከናውኑ ተገልጿል።

በጦርነት ከፍተኛ ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች አገልግሎቱን እንደሚሰጡ ተመላክቷል፡፡

በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ 192 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ የልማት ስራዎች ለማከናወን መታቀዱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version