Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሐረር ከተማ የቀጣይ 10 ዓመት መዋቅራዊ ፕላን ፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የሐረር ከተማ የቀጣይ 10 ዓመት መዋቅራዊ ፕላንን አፅድቋል።

መዋቅራዊ ፕላኑ ከዚህ ቀደም የነበረው የከተማ ፕላን የአገልግሎት ጊዜው በማለቁ እና የከተማዋን እና የክልሉን አሁናዊ ሁኔታ በዝርዝር ጥናት ላይ በመመርኮዝ ለቀጣይ 10 ዓመታት የሚያገለግል አዲስ የከተማ መዋቅራዊ ፕላን መሆኑ ተገልጿል።

መዋቅራዊ ፕላኑ የሐረር ከተማን የዕድገት ደረጃ ለማሳደግ፣ በከተማና በገጠር ወረዳዎች የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት የሚፈታ እና ሁሉንም በእኩል የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም ከሐረር ከተማ በተጨማሪ ሌሎች የወረዳ ከተሞች እና የገጠር ወረዳ ማዕከላት እንዲፈጠሩ በማድረግ ወጣቶች በሚኖሩበት አካባቢ የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል መባሉን የሐረሪ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version