አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ 14ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
በጉባዔው ላይ÷ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አመራሮች እና የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የበጀት አመቱ የጉባዔው የሥራ አፈጻጸም እንዲሁም የኦዲትና የፋይናንስ አጠቃቀም ሪፖርት በጉባዔው እንደሚቀርብ ይጠበቃል።
የጉባዔው የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ እና የአሜሪካ የልማት ተራድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤድ) ፕሮጀክት ዕቅድ ላይ ውይይት ተደርጎ እንደሚጸድቅ ተመላክቷል፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

