አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰብዓዊ እርዳታ ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ብር መያዙን በአፋር ክልል የጉምሩክ ኮሚሽን የሠመራ ቅርጫፍ ሰርዶ መቆጣጠሪያ ጣቢያ አስታውቋል፡፡
የጣቢያው አስተባባሪ ኮማንደር አሕመድ ሳልህ በፍተሻ ጣቢያው በሕገወጥ መንገድ የሚዘዋወር ነዳጅና ጥሬ ገንዘብን ጨምሮ የተለያዩ ቁሳቁሶች እየተያዙ መሆኑን ጠቁመው÷ ባለፈው ሳምንትም በጣቢያው በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ8 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ መያዙን አስታውሰዋል፡፡
ዛሬ ጠዋት 3 ሰዓት ላይ ደግሞ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ3-A10298 የተሳቢ ሰሌዳ ቁጥር 23634 በሆነ ከባድ ተሽከርካሪ ውስጥ 2 ሚሊየን 280 ሺህ 640 ብር እና የወርቅ ሚዛን መያዙን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
ተሽከርካሪውና አሽከርካሪው በሕግ ቁጥጥር ስር ውለው ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

