Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ወደ 2ኛ ምዕራፍ በሚንደረደርበት ሰዓት የሚዲያ ተቋማት በስፋት መገንባታቸው ወሳኝ ነው -ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ወደ ሁለተኛ ምዕራፍ በሚንደረደርበት ሰዓት የሚዲያ ተቋማት በስፋት መገንባታቸው ወሳኝ መሆኑን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገለጹ፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በደሴ ከተማ ባስገነባው ህንጻ ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ወደ ሁለተኛ ምዕራፍ በሚንደረደርበት ሰዓት የሚዲያ ተቋማት በስፋት መገንባታቸው ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኮሚሽኑ የሚያከናውናቸው ተግባራት ህዝቡ ዘንድ የሚደርሱት በሚዲያና በተግበቦት መሆኑን ጠቁመው÷ለዚህም የመገናኛ ብዙሃን ሚና ከፍተኛ መሆኑን አውስተዋል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም ኮሚሽኑ የሚያስተላልፋቸውን መረጃዎች ለህዝቡ ተደራሽ እንደሚያደርግ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ስራ ስኬታማነትም ሁሉም ዜጋ በአንድነት እና በቅንጅት እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ለደሴ ከተማ ህዝብና ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሰራተኞችም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version