አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የልዑካን ቡድን በምሥራቅ ሸዋ ዞን ቦራ እና ዱግዳ ወረዳዎች በኩታ ገጠም የለማውን የስንዴ ማሳ ጎብኝቷል።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የስንዴ ምርት ለማሳደግና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ብሎም ከውጭ የሚመጣውን ስንዴ ለማስቀረት በትኩረት እየሠራ መሆኑ ተገልጿል።
በምሥራቅ ሸዋ ዞን በዘንድሮ የመኸር እርሻ 439 ሺህ 120 ሔክታር እየለማ ሲሆን÷ ከዚህም 184 ሺህ 309 ሔክታሩ በኩታ ገጠም የስንዴ ሰብል የለማ መሆኑን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡
በስንዴ ልማት የተያዘውን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ የአርሶ አደሩን ግንዛቤ በማጎልበት በተከናወነው ሥራ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

