Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሶማሊያ ጦር በወሰደው እርምጃ 6 የአልሻባብ ታጣቂዎች ተገደሉ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 4፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሊያ ጦር ልዩ ሀይል በወሰደው እርምጃ ስድስት የአልሻባብ ታጣቂዎች መገደላቸው ተሰማ።

የጦር ሀይሉ እርምጃውን የወሰደው በቅርብ ጊዜ ማንዴራ ውስጥ በአልሻባብ ታጣቂዎች በተሰነዘረ ጥቃት ሁለት ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

ከተገደሉት ስድስት በተጨማሪ አንድ የሽብር ቡድኑ አባል ቆስሎ በህይወት መያዙም ነው የተገለጸው፡፡

የአካባቢው ኮሚሽነር ኒኮላስ ናዳላና የተያዘው አባል የህክምና ክትትል እየተደረገለት መሆኑን ጠቁመው÷ ለምናደርገው ምርመራ እገዛ ያደርጋል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

የታጣቂ ቡድኑ በአካባቢው የሚያደርሰው ተደጋጋሚ ጥቃት ለነዋሪዎቹ ትልቅ ችግር እየሆነ መምጣቱም ነው የተነገረው፡፡

በአሁኑ ወቅት አካባቢው በፖሊስ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገበት መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ የሽብር ቡድኑ በአካባቢው ባደረሰው ጥቃት የ20 ንጹሃን ዜጎች ህይወት ማለፉን መረጃዎች መለክታሉ፡፡

 

ምንጭ፡-ዴይሊ ኔሽን

 

Exit mobile version