አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስምንት ቀናት 127 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ከሐምሌ 21 እስከ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው ዘመቻ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 14 ሰዎችንም በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡
እንዲሁም በተጠቀሱት ቀናት 127 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡
ከዚህ ውስጥ 118 ነጥብ 5 ሚሊየን የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች ሲሆኑ ÷ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ደግሞ የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች ናቸው፡፡
በዚህም የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት አቃቂ ቃሊቲ ፣ አዲስ አበባ ኤርፖርት ፣ እና ምያሌ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከልም አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት ፣ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች እንደሚገኙበት ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

