Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ሙስጠፌ ከክልሉ ወጣቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ከክልሉ ወጣቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ ፡፡

የውይይት መድረኩ የክልሉ ወጣቶች በወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ላይ በሚኖራቸው ሚና እና ለወጣቱ ከሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ያለውን እውነታ ግንዛቤ ለመስጠት ያለመ እንደሆነ መገለጹን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ውይይቱን አስመልክቶም የሀገርና የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ለማጠናከር የጸጥታ የአቋም መግለጫ አስቀመጥዋል፡፡

በዚህም ከሀገሪቱና ከክልሉ ጸጥታ አካላት ጋር በተቀናጀ ለመስራትና ለመተባበር ቃል እንገባለን፣የክልሉ መንግሥትና የጸጥታ ኃይሎች በወራሪውና አሸባሪው የአልሸባብ ቡድን ለመከላከልና ለማጥፋት የተሰጠውን ምላሽና በተደረገው ስልታዊ የተቀናጀ ዘመቻን እናደንቃለን፤አሸባሪዎች በሀገራችንና በክልላችን ላይ ያደረገውን ሙከራና የፈሪ ጥቃት እናወግዛለን ብለዋል።

እንዲሁም የህዝቡን ሰላምና መረጋጋት ለማደፍረስ የሚሞክሩ ጸረ-ሰላም ሃይሎች ከመንግስት ጋር በመሆን ወጣቱ በጋራ እንዲከላከል እንጠይቃለን ያሉ ሲሆን÷ ከዚህ በተጨማሪም የሶማሌ ክልል ወጣቶች በሀገሪቱና በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የክልሉን ብሎም የሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ለማደፍረስ የሚሞክር ማንኛውንም ጠላት ለመመከት በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

በመድረኩ አቶ ሙስጠፌን ጨምሮ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙበሽር ድባድ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ሁሴን ሃሺ ቃሲም፥ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ማህዲ እና ሌሎች የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ።

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version