Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጎንደር ከተማ አደንዛዥ እጽ ሲያዘዋውሩ ተገኝተዋል የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ 52 ኪሎ ግራም የሚመዝን አደንዛዥ እጽ ሲያዘዋውሩ ተገኝተዋል የተባሉ ሁለት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር እየሩስ አስማረ እንደገለጹት÷ አደንዛዥ እጹ በከተማው ቀበሌ 01 ልዩ ቦታው ብልኮ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ነው በዛሬው ዕለት የተያዘው፡፡
አደንዛዥ እጹ በባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ በድብቅ ተጭኖ ሲጓጓዝ መያዙን ገልጸው÷ አሽከርካሪውን ጨምሮ አደንዛዥ እጹን ሲያጓጉዙ የተገኙ ሁለት ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ባደረገው ክትትል አደንዛዥ እጹ መያዙን ጠቁመው÷ ህብረተሰቡ ለፖሊስ ስለሰጠው ጥቆማ አመስግነው በቀጣይም የተለየ ነገር ሲያጋጥም የተለመደ ትብብሩን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።
በከተማው በሚስተዋለው የእፅ ዝውውር ትውልዱን ከሱስ ተጋላጭነት ለመታደግ ወንጀሉን ከመከላከል ጎን ለጎን ወላጆች ለልጆቻቸው ተገቢውን ክትትል በማድረግ ደኅንነታቸውን የመጠበቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ዋና ኢንስፔክተር እየሩስ አሳስበዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version