Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሸባሪው ህወሓት የሰላም አማራጮችን እንዲቀበል ግፊት ሊያደርግበት ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሓት የሽብር ቡድን ከፀብ ጫሪ ድርጊቱ በመውጣት የሰላም አማራጮችን እንዲጠቀም የትግራይ ህዝብና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግፊት ሊያደርግበት እንደሚገባ ምሁራን ገለጹ፡፡
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ጥናት ባለሙያ ንጋቱ አበበ የማድረግ አቅሙ ከፍ ያለው የፌዴራል መንግስት ለሰላም ቁርጠኝነቱን ሲገልፅ ፥ ባልተለመደ መልኩ የማድረግ አቅሙ ዝቅተኛ የሆነው ህወሓት ቅድመ ሁኔታዎችን ማብዛቱ ዛሬም ከአሳሳች መንገዱ ላለመውጣቱ ማሳያ ነው ብለዋል።
የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ዶክተር ደጉ አስረስ በበኩላቸው፥ ለንግግር ራስን ማዘጋጀትና ህዝብን ያስቀደሙ ስራዎችን ስለሰላም መስራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን የፌደራል መንግስት ለሰላም ብዙ ርቀት ቢጓዝም በህወሓት የሽብር ቡድን በኩል አሁንም የሄድ መለስ ፖለቲካ እንደሚስተዋል ይናገራሉ፡፡
መንግስት የሰላም አማራጮችን ለመከተል የባለሙያዎች ቡድን ማደራጀቱንና የተለያዩ ስራዎች መጀመሩን መግለፁ ይታወሳል፡፡
በአፈወርቅ እያዩ
 
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
Exit mobile version