Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጎርፍ አደጋ የስድስት ሰዎችን ሕይወት ቀጠፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምሥራቅ ጎጃም ዞን አዋበል ወረዳ እና በሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ  በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የስድስት ሰዎች ሕይወት አለፈ።

በምሥራቅ ጎጃም ዞን አዋበል ወረዳ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ፥ በወረዳው የሚኖሩት አባዎራ ከባለቤታቸው እና ልጃቸው ጋር ስራ ውለው ሲመለሱ በአካባቢው የሚገኘው ወንዝ በጎርፍ በመሙላቱ ለመሻገር ሙከራ እያደረጉ ባለበት ወቅት በወንዙ መወሰዳቸው ተገልጿል፡፡

በአደጋው የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ከአዋበል ወረዳ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ በሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ በጎርፍ አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በተከዜ ወንዝ መነሻ ላይ በአደጋው ሕይወታቸው ካለፈው ሰዎች ሁለቱ፥ የአንድ ቤተሰብ አባላት ሲሆኑ አንዱ ከአጎራባች ወረዳ ለማኅበራዊ ጉዳይ በስፍራው የተገኘ መሆኑን አሚኮ ዘግቧል።

ለተከዜ ወንዝ መነሻና ለገባሮቹ መሻገሪያ ድልድይ ባለመኖሩ የዛሬዎቹን ጨምሮ በየዓመቱ የብዙ ወገኖችን ሕይወት እንደሚያልፍ

የግዳን ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ታምራት ንጋቱ ገልጸዋል።

ዜጎች ክረምቱን ተከትሎ የሚከሰትን ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ በጥንቃቄ ማለፍ እንደሚገባቸውም አሳስበዋል፡፡

 

 

Exit mobile version