አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አየር ኃይል የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚመጥንና በሕዝቡ ዘንድ የባለቤትነት ስሜት የሚፈጥር ማሻሻያ ማድረጉን ማየታቸው እንዳስደሰታቸው የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ኃላፊዎች ተናገሩ።
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እና የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አመቻችነት ከ50 በላይ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ኃላፊዎች የኢፌዲሪ አየር ኃይልን ጎብኝተዋል።
ጎብኝዎቹ እንደገለጹት÷ አየር ኃይል በ93 ዓመታት የታሪክ ሂደቱ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም ቢሆንም ባለፉት ሩብ ክፍለ- ዘመናት በሰው ኃይልና ትጥቅ እንዲዳከም ተደርጎ ነበር።
በመሆኑም ተቋሙ የኢትዮጵያን ታላቅነት በውል ተገንዝቦ ለሕዝቡ ታሪክ የሚመጥንና የባለቤትነት ስሜት የሚፈጥር ሪፎርም ማድረጉን ታዝበናል ሲሉ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
አየር ኃይሉ ታሪክ፣ ባህልና እሴቱን ጠብቆ ለትውልድ የሚተላለፍ የሕዝብ ሀብት መሆኑን አሳይቷልም ነው ያሉት።
የፖለቲካ ፓርቲ ኃላፊዎቹ የተደረገው ተቋማዊ ሪፎርም በሕዝቡ ዘንድም እምነት የሚጣልበት ተቋም እንዲሆን ያስችለዋል ብለዋል፡፡
የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ እንደገለጹት÷ ተቋሙ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት የሰው ኃይሉንና የቴክኖሎጂ አቅሙን በማሳደግ የኢትዮጵያን አየር ክልል በንቃት እየጠበቀና እየተከላከለ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!