አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሚቀጥሉት አራት አመታት ጥራት ላይ በማተኮር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ።
የዚህ አመት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዛሬ በድሬዳዋ በተካሄደ መርሃ ግብር ተጠናቋል ።
በመርሃ ግብሩ ላይም “አረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያውያን የተናገርነውን ፈጽመን ያቀድነውን ተግብረን በፍጻሜ ላይ የምንቆም መሆናችንን ያረጋገጥንበት ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በአራት አመታት 20 ቢሊየን ችግኞች ለመትከል ታቅዶ 25 ቢሊየን ተሳክቷል ብለዋል።
በአራት አመታት በአረንጓዴ አሻራ 25 ቢሊየን ችግኞች መተከላቸው በእጅጉ የሚያኮራ እና የኢትዮጵያን ጀግንነት ያሳየ ነው።
በአልዓዛር ታደለ

