Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሕዝብን ሊጠቅም የሚችል ሃሳብ ለመቀበል ዝግጁ ነን – አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል መንግስት ሕዝብን ሊጠቅም የሚችል ማንኛውንም ሃሳብ ለመቀበል ዝግጁ  ነው ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር  አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ፡፡

በሲዳማ ክልል የዞን አደረጃጀት ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በተገኙበት እየተካሄደ ነው፡፡

በውይይት መድረኩ አቶ ደስታ ሌዳሞ እንደገለጹት÷ በክልሉ የዞን አደረጃጀት ለማዋቀር ኮሚቴ ተዋቅሮ ጥናት ተካሂዷል።

የዞን አደረጃጀት ጥናት ኮሚቴ ሰብሳቢና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ በየነ በራሳ በበኩላቸው÷ ጥናቱ ሲካሄድ የዞን መዋቅር የሚዋቀሩባቸው አከባቢዎች የህዝብ ተጠቃሚነት በሚገባ ሊያረጋግጥ በሚችል መልኩ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ውይይቱ  ከክልል፣ ከከተማና ከወረዳ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ከምሁራን ጋር የተደረገ መሆኑን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version