አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሀመድ በ600 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባውን ቪታ የታሸገ ውሃ ማምረቻ ፋብሪካ የማስፋፊያ ግንባታ መርቀዋል፡፡
የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው ቪታ የታሸገ ውሀ ማምረቻ ፋብሪካ÷ በሲቲ ዞን ሽንሌ ወረዳ በመርመርሳ ቀበሌ ነው የማስፋፊያ ግንባታው የተከናወነው፡፡
በምረቃ ስነ ስርዓቱ እንደተገለጸው÷ በቀን 50 ሺህ ካርቶን የታሸገ ውሀ የሚያመርተው ፋብሪካ ለ500 ዜጎች የሥራ እድል ፈጥሯል፡፡
40 ከመቶ ምርቱን ወደ ውጭ በመላክ የውጪ ምንዛሪ እያስገኘ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
አቶ ሙስጠፌ መሀመድ እንደገለጹት÷ ፋብሪካው የማስፋፊያ ፕሮጀክት ለህብረተሰቡ የሚያበረክተው አስተዋጽዖ ከፍተኛ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

