Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የግብርና ዕድገት ፕሮግራም ዓላማ እንዲሳካ በትኩረት መሥራት ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ዕድገት ፕሮግራም ግቡን እንዲመታ የክልል አመራሮች ፕሮጀክቱን በትኩረት እንዲመሩ የግብርና ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

ሁለተኛው ምዕራፍ የግብርና ዕድገት ፕሮግራም 9ኛው የዐቢይ ኮሚቴ ስብሰባ እና ግምገማ ተካሂዷል፡፡

የግብርና ዕድገት ፕሮግራም ከጀመረበት እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ያለው አፈፃፀም መገምገሙን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

የግብርና ሚኒስትር ዑመር ሁሴን እንደገለጹት የፕሮግራሙን አፈፃፀም መገምገም÷ ቀጣይ የሥራ አቅጣጫ ማስቀመጥ እና አዲሱ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ላይ ግብዓት መሰብሰብ ነው፡፡

የግብርና ዕድገት ፕሮግራም በአርሶ አደሮች ላይ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ዓላማው አድርጎ በመነሳት አበረታች ሥራ ሠርቷል ብለዋል፡፡

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን÷ የግብርና ዕድገት ፕሮግራም የቆይታ ጊዜው ከ2007 እስከ 2012 ዓ.ም ቢሆንም ቀሪ ሥራዎችን ለማጠናቀቅ ለ15 ወራት መራዘሙን ተናግረዋል፡፡

Exit mobile version