አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በክልሉ መንጌ ወረዳ ከሻፍ ቀበሌ የወርቅ ማምረቻ ማሽን መርቀው ከፍተዋል፡፡
ማምረቻ ማሽኑ በቤኒሻንጉል የማዕድን ዘርፍ ልማት ማኅበር የመጀመሪያው የወርቅ ማምረቻ ማሽን ነው ተብሏል፡፡
የወርቅ ማምረቻና ማጠቢያ ማሽኑ ባህላዊ የወርቅ ምርቱን ለማዘመን ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ነው መባሉን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!