አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩሮ የገንዘብ ምንዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ከአሜሪካ ዶላር በታች መሆኑ ተገለጸ፡፡
ለዩሮ የገንዘብ ምንዛሬ ዝቅ ማለት በሃይል ዘርፍ ያለው ቀውስ መባባስ እና አሜሪካ የገንዘብ ፖሊሲዋን በይበልጥ ጥብቅ ማድረጓ አበይት ምክንያት ነው ተብሏል፡፡
አሁን ላይ አንድ ዩሮ በ0 ነጥብ 9953 ዶላር የሚመነዘር ሲሆን ፥ከሐምሌ ወር አጋማሽ ጀምሮ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መድረሱም ተመላክቷል።
በዓለም አቀፉ የፋይናንስ ተቋም የገበያ ኃላፊ ክሪስ ተርነር እንዳሉት ፥ የዩሮ የገንዘብ ምንዛሬ በሃይል አቅርቦት ላይ በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት ተጎድቷል፡፡
ከዚህ ባለፈም በጋዝ አቅርቦት ላይ ሊፈጠር የሚችለው ችግርም የዩሮ ምንዛሬ ላይ ጥላውን እንዳጠላበት የጀርመኑ ጋዜጣ ሃንድልስብላትን ጠቅሶ የዘገበው ሺንዋ ነው፡፡
ጋዜጣው አክሎም ከፈረንጆቹ ነሐሴ 31 እስከ መስከረም 2 ባለው ጊዜ ውስጥ በኖርድስትሪም 1 የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር በኩል ወደ አውሮፓ የሚደርሰውን የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦት ጋዝፕሮም በጥገና ምክንያት እዘጋለሁ ማለቱም ለባለሀብቶች ስጋት መፍጠሩን አስነብቧል፡፡
ሌላው ለዩሮ የገንዘብ አቅም መውረድ በምክንያትነት የተቀመጠው የአሜሪካ ፌዴራል ሪዘርቭ የወለድ ተመን ፖሊሲ ነው ያለው የጀርመን የህዝብ ብሮድካስቲንግ ነው።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

