አዲ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ላሊበላ ከተሰጡን ጸጋዎች መካከል አንዷ በመሆኗ የቱሪዝም ማዕከል እና የዓለም ሕዝብ መዳረሻ ለማድረግ እንሠራለን ሲሉ አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡
የአሸንድዬ በዓል በላሊበላ ከተማ “አሸንድዬ የማንነታችን እና የአንድነታችን መስተጋብር ነው” በሚል መሪ መልዕክት በድምቀት ተከብሯል።
በበዓሉ አከባበር ላይ፥ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ እንዲሁም የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን በበዓሉ አከባበር ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ላሊበላ አሁንም ድረስ ዓለም የሚደመምበት እና ኢትዮጵያ ይበልጥ የምትታወቅበት ውብ የኪነ ጥበብ ማዕከል ነው ብለዋል፡፡
ታሪክን ማውሳት ብቻውን በቂ ባለመሆኑ ይህን ድንቅ የታሪክ፣ የባህል፣ የሃይማኖት እና የቀደምትነት ማዕከል ይበልጥ አልምቶ ሕዝብንም ሀገርንም ተጠቃሚ ማድረግ በዚህ ትውልድ ትከሻ ላይ ያረፈ ኃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል።
ልደትን ትናንት እና አሸንድዬን ዛሬ በአደባባይ ወጥተን እንድናከብር የሕይወት እና የአካል መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች እና ለሃይማኖት አባቶች ክብር እና ፍቅር አለን ብለዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ በበኩላቸው፥ የማንነት መገለጫ የሆኑ በዓላትን ለዓለም ማስተዋወቅ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
አንደኛው ድኅነትን የመታገያ መንገድም ቱሪዝምን በማስፋፋት፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ በዓላትን በአግባቡ በመንከባከብ ማንነትን በሚገልጽ መልኩ ማሳደግ እና የገቢ ምንጭ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
ያለ ሰላም በዓላትን ማክበርና ውብ የሆነውን ሃይማኖታዊና ባህላዊ ሥርዓትን ለዓለም ማሳየት እንደማይቻል በመጠቆም፥ እያንዳንዱ ዜጋ ሰላምን የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የአሸንድዬ በዓል በኮሮና ወረርሽኝ እና በአሸባሪው የትህነግ ወረራ ምክንያት ላለፉት ሁለት ዓመታት ሳይከበር መቆየቱ ተገልጿል፡፡
በክልሉ የሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል፣ ቡሄና የእንግጫ ነቀላ በዓል ከነሐሴ 16 ጀምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት እየተከበረ ሲሆን እስከ ነሐሴ 21 ድረስ እንደሚቀጥል ነው የተገለጸው፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

