አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔ በአዲስ አበባ የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
በጉባዔው ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) እና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ታዛቢዎችና የጠቅላላ ጉባዔው አባላት ተገኝተዋል።
በጉባዔው መክፈቻ የ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ነው።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ነገ እንደሚካሄድ የእግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!