አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጃፓን ለአፍሪካ 30 ቢሊየን ዶላር እርዳታ ለመስጠት ቃል ገባች።
በቱኒዚያ የጃፓን አፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ንግግር ያደረጉት የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ፥ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የምግብ እህል እጥረት መከሰቱን ገልጸዋል፡፡
ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ ሀገራቸው እህልና ጥራጥሬ ለአፍሪካ እንዲደርስ በትኩረት ትሰራለች ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ 30 ቢሊየን ዶላሩ በሦስት ዓመታት ውስጥ እንደሚደርስም ነው የገለጹት።
በአፍሪካ በምግብ ሰብል ራስን ለመቻል ለሚደረገው ጥረት ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በትብብር ትሰራለች ማለታቸውንም ሬውተርስ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

