Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአቶ አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ በሶማሌ ክልል የልማት ሥራዎችን ጎበኘ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ የአመራሮች ልዑካን ቡድን በሶማሌ ክልል ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተሠሩ የልማት ሥራዎችን ጎበኘ፡፡

በጉብኝቱ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ልዑካን ቡድኑ በጅግጅጋ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን መጎብኘቱን የሶማሌ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

በጅግጅጋ ከተማ የተገነቡ የመንገድ፣ የውሃ፣ የመሠረተ ልማት አውታሮች፣ አገልግሎት መስጫ ህንፃዎች፣ የግብርና ውጤቶች፣ የችግኝ ማፍያ ጣቢዎች እንዲሁም ሌሎች የልማት ሥራዎችን ጎብኝቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version